የሲዳማ የግጭት አፈታት ሂደት ሀገር በቀል እውቀቶች ለዘመነው ማህበረሰብ ምሶሶዎች ናቸው፡፡ ከዚህም ውስጥ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች በዋነኝነት የጠቀሳሉ፡፡ ይህም በባህል ዘውግ መሰረት ሰዎች ባልተሰማሙባቸው አውዶች ላይ እርቅን መፍጠር የሚፈፀሙ ሸንጎዎችንና ባህላዊ ግጭቶች አፈታት ስነ-ስረዓቶች ሀገር በቀል እውቀት በመሆናቸው ከዘመናዊ ከፍርድ ቤት የዳኝነት ስረዓት የተለዩ ናቸው፡፡ የሲዳማ ህዝብ እንደ ማህበረሰብና እንደ ትውልድ ለዘመናት ጠብቆና ተንከባክቦ ያቆየው የራሱ የሆነ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ አለው፡፡ በዚህ የግጭት አፈታት አውድ ውስጥ ′′አፊኒ′′ (በግጭት አፈታት ስነ-ሥረኣት ውስጥ ሀሳብን የማንሸራሸር ስልት) ዋነኛው ነው፡፡ ይህም ቀጥተኛ የአማርኛ ትርጉሙ ′′ሰማችሁ ወይ′′ እንደማለት ነው፡፡ አፊኒ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ግለሰቦች ወይም አካሎች በሸንጎ ውስጥ በውይይት ወይም በውሳኔ አሰጣጥ እንዲሳተፉ እድል የሚሰጥ መንገድ ነው፡፡ ሀሳብን ለማንሸራሸርና ለማሳሰብ ግዜ ለማግኘት ጭምር የሚረዳ የንግግር መሳሪያ ነው ማለት ይቻላል