Skip to main content
sp

ሲዳማ እንግዳውን "ዳዎኤ ቡሹ" ብሎ ይቀበላል። ይህ በአማርኛ አቻው እንግዳዬ እንኳን ደህና መጣህልኝ ከሚለው መልዕክትም ይዘላል።

‎በዚህ ቃል ሲዳማ ጥልቅ ፍቅርን የሚገልፅበትም ሆኖ "እኔ አፈር ይምጣብኝ" እስከማለት የዘለለ እውነታን ነው።

‎ከ'ዳዎኤ ቡሹ' ሲልቅ ህዝባችን "ሱቁ ሱሩሩ ዳዎኤ" ይላል!!!

‎የዋህ፣ ጨዋነት ምግባሩ፣ እና አብሮነት ፍቅሩ የሆነ ህዝባችን በዘፈቀደ አይጠራውም ይህን ቃል። አቅፎ ሲስም ከልቡ ነው!!!

‎ያለውን ሲያቀርብም ጓዳውን ሳይጠይቅ ነው። እኛም እንላለን "ቡሹ ዳዎኤ" አኔራ ዳዎኤ ቡሹ"

ኑ! አብረን በሻፌታ አብሮነታችንን እንቋደስ!!!

Comments