
ወ/ሮ መቅደስ ሁሪሶ
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የባህልቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ
መልዕክት
ውድ የሆነውን የመዝናኛና የእርፍት ጊዜዎን በምርጧ ከተማ -ሀዋሳ ያድርጉ፡፡
ሀዋሳ ከተማ በ1952 ዓ.ም በታላቁ የምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘውን የሀዋሳ ኃይቅን ተንተርሳ ከአዲስ አበባ በ275 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተመሰረተች ከተማ ነች፡፡ ከተማዋ በፈጣን ልማትና እድገት ውስጥ የምትገኝ በቀጠናው ተመራጭ የመዝናኛ፣ የንግድና የኢንቨስትመንት መዳረሻ ነች፡፡
ሀዋሳ ለተዝናኖት ምቹ የአየር ንብረት እና የተፈጥሮ ገጽታዎችን ከመላበሷም በተጨማሪ በቂ የመሰረተ ልማቶች፣ ማህበራዊ ልማቶች፣ ጠንካራና ሁሉን ማስተናገድና ተሳታፊ የሚያደርጉ ማህበራዊ መስተገብሮች እንዲሁም የጋለ የቀን ተቀን የኢኮኖሚና የዜጎች እንቅስቃሴ የሚስተዋልባት ከተማ ነች፡፡ ሀዋሳ ሁሉ አቀፍ የትራንስፖርት አማራጮች ያሏትና የመገናኛ አውታሮች የተሟሉላት ምቹ ከተማ ነች፡፡
ሀዋሳ ዘመን ጠገብ ባህላዊ ትውፊቶች እና ቅርሶች የሚስተዋሉባት ከተማ መሆኗ ልዩ ያድረጋታል፡፡ በዚህም የተነሳ በከተማዋ እጅግ በርካታ የሆኑ መንፈሳዊና ማህበራዊ ሁነቶችን በተለይ አለም አቀፍ እውቅና ያገኙት እንደ ፍቼ ጨምበላላ የሲዳማ ህዝብ ዘመን ወለወጫ በአል፣ የጥምቀት በአል እንዲሁም በአመት ሁለት ግዜ በታህሳስና ሐምሌ የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል በአላት፣ አመታዊ የእስልምና በአላት፣ የፕሮቴስታንትና የተለያዩ ቤተ- እምነቶች የሚከውኗቸውን ታላላቅ በአላት የምታስተናግድ በመሆኗ የእረፍት ጊዜን የእነዚህን ትላልቅ ሁነቶች የጊዜ ሰሌዳ በማስላትና ታሳቢ በማድረግ በሀዋሳ ከተማ በመገኘት እነዚህን አጋጣሚዎች መጠቀምና ታላቅ ተዝናኖትን ማግኘት ይቻላል፡፡ በእነዚህ መሰል ታላላቅ በአላት መገኘት የሀገሪቱን ዘመን ጠገብ ማህበራዊ መስተጋብሮችና ባህልም ለመረዳትና ለማወቅ በእወናዊ ቦታው መገኘትን ያጎናጽፋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በሀዋሳ የሚስተዋለው ሌላው እድል የህብረተሰቡ እንግዳ ተቀባይነትና እንክብካቤ ነው፡፡ ሀዋሳ ለማንኛውም ሰው የቤትን ያክል የምትደላ ከዛም ጋር ተያይዞ እንግድነት የማይሰማባት ከተማ ናት፡፡ በዚህ የተነሳ ሀዋሳ እጅግ ሰላማዊና ለእንግዶቿውም ይሁን ለነዋሪዎቿ አስተማማኝ ከተማ ናት፡፡
Mision

Vision

Values

Services
Attractions development,
studies and promotion